Welcome to Ethio Agri-CEFT Plc

The Voice of Ethio Agri-CEFT

NEWS

በኢትዮ አግሪ-ሴፍት /ዋና ሥራ አስኪያጅ የሚመራ የልኡካን ቡድን በኬንያ የስራ ጉብኝት አደረገ

ቡድኑ  ከአፍሪካ  ሀገራት   የአበባ   ምርት  በማልማትና  ለዓለም  ገበያ በማቅረብ   ቀዳሚውን ስፍራ በያዘችው ሀገረ ኬንያ  በመገኘት በአበባ  አብቃይ እና የዝርያ አዳቃይ እርሻዎች  (Rose and Summer Flower Growers  and Breeders) በተለያዩ  የአበባ  ዝርያዎች  ምርታማነት  ላይ  እየተከናወኑ  ያሉ  ውጤታማ ተግባራትን  ጎብኝቷል።

የልዑካን ቡድኑ   ከየካቲት 10-15/2017  ..   በናይቫሻ  እና  ናከሩ   ከተሞች  በተካሄደው  የአበባ  እርሻዎች  ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ መርሃግብር  መሰረት  ሰባት  የአበባ እርሻዎችን (Danziger summer flowers and rose breeders,  Dummen  Orange,   United Selection,  Schreurs rose breeders,  Rosen Tantau rose breeders,  De-Ruifter rose breeders,  Inter plant rose breeders)   የጎበኘ ሲሆን አዳዲስ የተለያዩ ቀለማት ያላቸው  የጽጌረዳ አበባ ዝርያዎች  ያላቸውን ተስማሚነት፣ የገበያ አቅም  እንዲሁም  ከኩባንያው  እቅድ ጋር የሚጣጣሙትን  ለመምረጥ  ያገዘ ከመሆኑም በላይ  የአበባ  አመራረት ዘዴዎች  ላይ የተሻሻሉ ተሞክሮዎችን  እንዲወስዱ  አድርጓል፡፡

የልኡካን ቡድኑ ከዚህ ጉብኝት ካገኛቸው ምርጥ ተሞክሮዎች  በመነሳት የኩባንያውን የአበባ ምርቶች ወደ መላው ዓለም ለማዳረስ የበለጠ  አቅም እንደፈጠረለት ተመልክቷል፡፡


ኢትዮ አግሪ-ሴፍት . የተ. የግል ማኀበር Zambia Seed Company Limited (ZAMSEED)ባዘጋጀውልምድ ልውውጥ ላይ ተሣተፈ

ኢትዮ አግሪ-ሴፍት . የተ. የግል ማኀበር  በምርጥ ዘር አመራረት እና በዘላቂ የግብርና ልምዶች  የሚታወቀው  ZAMSEED   ኩባንያ ባዘጋጀው የምርጥ ዘር  እርሻዎች ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ ላይ ተሳተፈ፡፡

ከየካቲት 11-15/2017 .በተካሄደው  የእርሻዎች ጉብኝትና የልምድ ልውውጥ መርሃግብር መሰረት  ምርጥ ዘር በቆሎ ያለበት ደረጃ እንዲሁም በዘር አመራረት ሂደት ውስጥ ያሉ ምርጥ ልምዶች፣ ጥሩ ምርትን ለማረጋገጥ የጥራት ቁጥጥርን አስፈላጊነት መረዳት፣ በአጠቃላይ የተሸለ ተሞክሮዎችን  እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡

ኩባንያው በተሰማራበት የግብርና ዘርፍ ዘላቂ እድገት እንዲኖር በትኩረት እየሰራ ባለበት ወቅት  ከዚህ ጉብኝት ካገኛቸው ምርጥ ተሞክሮዎች መካከል አንዳንዶቹን በራሳችን ኦፕሬሽኖች በማዋሃድ ፈጠራን እና በግብርና ተግባሮቻችን ላይ  እገዛ እንደሚያደርግ ይታመናል፡፡

×